አዲስ አበባ የተበላች ዕቁብ!!
(ኤልያስ በቀለ)

አማራ ተስፋው መደራጀት ብቻ ነው ! አንድ መሆን ብቻ ነው! ማንም በሚቀርጽለት ፕሮግራም ሳይሆን የራሱ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ፣ ማህበራዊና የሴኪውሪቲ ፐሮግራም ቀርጾ መንገዱን አንድ ብሎ መጀመር አለበት ! ዛሬ እየተንጋጋ የገባው የኦነግ ሰራዊት አገር ብቻ ነው የቀየረው አስተሳሰቡ ያው የትላንቱ ነው!አማራ ጠል!! ዘረኛ ! ኢትዮጲያ የሚል ስም የሚያቃዥው !! በኦነግና በቄሮ መካከል ያለው ልዩነት ምን ይመስልሃል? ምንም! ቄሮ መሳሪያ ያልታጠቀ ኦነግ ነው! ዛሬ በዱላ የዛተባትን አዲስ አበባ ነገ ነፍጥ ተሸክሞ ይመለስባታል!ዛሬ ማፍረስ ነበር ብሎ የተመለሰውን የሚኒሊክ ሃውልት ብቻ ሳይሆን እየተግተለተለ አንኮበር ልዝመት ይላል!! ያኔ በዳቦና በውሃ የምትመልሰው ከመሰልህ ጅል ነህ! አዲስ አበባ የተበላች ቁብ ናት!!ዛሬ አንድም የአዲስ አበባ ነዋሪ ቀና በሎ ህገ መንግስቱ በፈቀደለት መሰረት በድፍረት አዲስ አበባ የራሳችን ናት ማለት አይችልም! መንግስትን ጨመሮ!!

ሁሉም ይሉኝታ ይዞት ሰላም ይሻላል ብሎ አገርና አንድነት የበጃል ብሎ መታገሱ አዲስ አበባን አስበልቶታል! ባሻው ጊዜ ብቅ እያለ የሚያስፈራራው ሃይል ተዘጋጅቶለታል! አሁን ህግ አስፈጻሚ ማለት ባኮረፈ ቁጥር ዱላ ይዞ መንገድ የሚዘጋው ቄሮ ነው! አሁን ፓርላማ ማለት ዝጉ ክፈቱ ግቡ ውጡ እያለ የሚያዘው ጃዋር ነው! ይሄን ሁላችንም እናውቃለን!! ችግሩ ይሄ ብቻ አይደለም የትግራይ አክቲቪስቶች የአዲስ አበባን ህዝብ ዶሮ ሳይጮህ ሶስት ጊዜ ክደውታል! ሴቶች ህጻናት ሚሊየኖች የሚኖርባት አዲስ አበባን ቄሮ በተባለ ቡድን እሳት እንዲለቀቅባት ከበው ድጋፍ ሲሰጡና ሲያጨበጭቡ፣ የሚኒሊክ ሃውልት እንዲፈርስ በዘወርዋራው ሲገፋፉ ደም እንዲፈስ ሲያጃግኑ እዚሁ ፌስቡክ ላይ አይተናል ! ይህ አዲስ አበባ ላይ የሞከሩት እልቂትና የደገሱት እልቂት ትላንት ደርግ ሃውዜን ላይ ፈጸመብን ካሉት ጭፍጨፋ አስር እጥፍ የሚበልጥ ነው!! አሁንም በአዲስ አበባ ዙሪያ ለሚደርሰው ግድያም ሆነ ዘረፋ እነዚህ አክቲቪስቶች ከቄሮ እኩል ተጠያቂ ናቸው !! የሆነ ሁኖ የዚህ ሁሉ ስንክሳር የመጀመሪያ ኢላማ የሆነው አማራ ከመደራጀት ውጭ ሌላ አማራጭ የለውም!

Advertisements

ኤልያስበቀለ

===============================

እውነቱን መነጋገር ካለብን ጊዜው አሁን ነው። ታሪክ አንዴ ከተጻፈ በኋላ ለመቀልበስ ዘመናትን ይፈጃል። አሁን በተዛባ መልኩ እየተጻፈና እየተነገረ ያለው የቄሮ ገድል በአዲስ አበባና በአጠቃላይ በሀገሪቱ ለተከሰተው ውጥረት መነሻ ሆኗል። የቄሮ ትግል መቼ ጀመረ? ዓላማው ምን ነበር? እነማን ምን አደረጉ? የሚሉትን ጥያቄዎች አንስተን ሀቁን በማፍረጥረጥ መነጋገር መቻል አለብን። ሁላችንንም ሀገር ያሳጣን፡ ነጻነትና ፍትህ የነፈገን አንድ የዘረኛ ስርዓት ለማስወገድ የውስጥ ሹኩቻዎችን፡ የጎንዮሽ ትግሎችን ወደጎን ማድረጉ ተገቢ ነበር። ተደርጓልም። ቢያንስ በእኩልነት በህግ የበላይነት አብሮ ለመኖር የሚያስችል ዝቅተኛ የመግባቢያ መፍትሄ ላይ ያተኮረው የጥምረት ትግል ህወሀትን ከቤተመንግስት አፈናቅሎ ከመቀሌ እንዲመሽግ አድርጎታል።

የኢትዮጵያውያን የነጻነትና የፍትህ ተጋድሎ ቄሮ የሚባል ቡድን ከመጣ ወዲህ የተጀመረ አድርጎ ታሪክን በማጣመም ከእኛ በላይ ለአሳር በሚሉ የዘር ፖለቲካ አቀንቃኞች እጅ ላይ የኢትዮጵያ እድል እጣ ፈንታ ሊወድቅ አይገባም። አሁን የልብ ልብ ተሰምቷቸው፡ እኛ ባሰመርነው ካልሆነ አትንቀሳቀሱም የሚሉ ፈንዲሻ አክቲቪስቶች ስለቄሮ ትግል ሲነግሩን የለም ሀቁ እንዲህ ነው ብሎ መጋፈጥ ለቀጣይ እውነተኛ መፍትሄ ለማምጣት የመጀመሪያው እርምጃ ነው። በነበርንበት፡ ከአይናችን ባልራቀ ዘመን የተፈጸመን የትግል ታሪክ እነሱ ሰፍተውና ጎንጉነው ለሁላችሁም ነጻነትን ያመጣነው እኛ ነው በሚል ትርክት ሲያደነቁሩን ሀገር ለማረጋጋት በሚል ሆደ ሰፊነት በጸጋ መቀበሉ ዋጋ እያስከፈለ ነው። ዛሬ ከ50 በላይ ወገኖቻችን ለአሰቃቂ ግድያ የተዳረጉት ይሀው ”ነጻነትን ያመጣንላችሁ እኛ ነን” በሚሉ የዘር ፖለቲካ አቀንቃኞች የተዛባ የትግል ትርክት ነው።

ስለቄሮ ትግል ዋጋ ማሳነስ አይገባም። አለመጥንም ተለጥጦ የተጠማነውን ነጻነት ይበልጥ እንድናጣው እስክንደረግ በይሉኝታ መቀበልም ለማናችንም አይበጅም። የኢትዮጵያ ትግል ከግማሽ ክፍለ ዘመን ወዲህ ያለውን ብንመለከት አያሌ መስዋዕትነት የተከፈለበት፡ በሀገሪቱ በአራቱም ማዕዘናት የኢትዮጵያ ልጆች ዘር ቀለም ሀይማኖት ሳይገድቧቸው የተዋደቁለት ትግል ተካሂዷል። ከ1953 መፈንቅለ መንግስት ጀምሮ የእነ ገርማሜ ነዋይና መንግስቱ ነዋይ ተጋድሎ፡ የ1966ቱ አብዮት፡ የ1997 ምርጫ ከብዙ በጥቂቱ የሚጠቀሱ የኢትዮጵያውያን የፍትህና የነጻነት ትግሎች ናቸው። የአዲ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በየጊዜው የሚያደርጉት ትግል የህወሀትን አገዛዝ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በማጋለጥ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ነበረው። በ1997 ምርጫ አዲስ አበባ 200 ልጆቿን ያጣችበትን ትግል ዘንግቶ የአዲስ አበባን ህዝብ መንቀፍ የሞራል ክስረት እንጂ ሌላ ስም አያሰጥም። አኝዋኮች የተጨፈጨፉበት፡ ሲዳማዎች በሎቄው ትራጄዲ ውድ ህይወታቸውን ያጡለት፡ ወልቃይቶች የዘር ማጽዳት ወንጀል ተፈጽሞ ማንነት የተነጠቁበት፡ ሌላም ሌላም።

የህወሀትን አገዛዝ ለመጣል አናቱን መምታት አስተዋጽኦ ነበረውና የአቶ መለስ ዜናዊ ህልፈትም ትግሉን በብዙ እጥፍ ወደፊት እንዲራመድ አድርጎታል። በዚህ ረገድ አቶ መለስ ዜናዊ ላይ በጋዜጠኛ አበበ ገላው የቀረበው ተቃውሞ የሚሊዮኖችን የትግል ወኔ ያነቃቃ እንደነበረ የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው። የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ከጫፍ እስከ ጫፍ የተሰለፉለት የሃይማኖት ነጻነት ትግል የህወሀትን ወንበር የነቀነቀ ነበር። የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ከእስርና ስደት እስከሞት ዋጋ የከፈሉለትን ትግል ማን ነው የሚዘነጋው? ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና ፖለቲከኛው አንዱዓለም አራጌ አቋማቸውን ሳይቀይሩ መልካቸውን ቀይረው የወጡበት ትግል እንዴት ይረሳል? የዞን ዘጠኝ ጦማሪውያን ከወጣትነት እድሜአቸው ተቀንሶ በግዞት ማሰቃያ እስርቤት የማቀቁት ለግል ጥቅማቸው መከበር ሲሉ አልነበረም። የኢትዮጵያ የ50 ዓመት ታሪክ እኮ በኢትዮጵያውያን እልህ አስጨራሽ ትግል የተሞላ ነው። ከዚያ ሌላ ምን የሚጻፍ ታሪክ አለ? ዛሬ ደርሶ ቄሮ ብቻውን የትግሉ ባለቤት ነው የሚለው ታሪክ ለምን አስፈለገ?

እውነት ለመነጋገር ህወሀት አከርካሪው ተሰብሮ ወደ መከላከል ደረጃ የወረደው በ1997 አዲስ አበባ ላይ ከተመታ በኋላ ነው። ከአምስት በላይ አፋኝ ህጎች የወጡትና ህወሀትም የለየለት ጸረ ዲሞክራት አገዛዝ የሆነው ከዚያን ወዲህ ነው። የመለስ ሞት ውድቀቱን አፋጠነ እንጂ ሕወሀት የቁልቁለት ጉዞውን የጀመረው አዲስ አበባ ላይ አይሆኑ ምት ከተመታ በኋላ መሆኑ መካድ አይገባም። ዓለምም የዚህን ዘረኛና ኋላ ቀር ስርዓት ባህሪ በመረዳት የነጻነት ትግሉን በተወሰነ ደረጃ መደገፍ የጀመሩት በ1997 የአዲስ አበባ ህዝብ በወሰደው ቆራጥ እርምጃ ህወሀትን ማጋለጡን ተከትሎ ነው። የአዲስ አበባ ህዝብ ውለታ መቼም የሚረሳ አልነበረም። ያኔ ቄሮ የሚባለው ሃይል በስም ደረጃ ስለመታወቁም እርግጠኛ አይደለሁም።

ባለፉት ሶስት ዓመታት በተደረገው ትግል የቄሮ ስም ከፍ ማለቱ እርግጥ ነው። በመላው የኦሮሚያ ክልል በተደረገው ትግል ቄሮ በወጉ ባይደራጅም፡ የሚታይ መሪ ባይኖረውም፡ የህወሀትን አገዛዝ ለመጣል ከፍተኛ መስዋዕትነት መክፈሉን ታሪክ መዝግባዋለች። ይሁንና ቄሮ ብቻውን አልነበረም። እዚህም እዚያም ኢትዮጵያውያን ውድ ዋጋ እየከፈሉ ከቄሮውች ጎን ለመኖራቸው የህይወት ምስክር ሆነን መናገር እንችላለን። እንደውም ያዝ ለቀቅ እያደረገ የነበረውን የቄሮን ትግል እንዲቀጣጠልና የህወሀትን ጎሮሮ ሰንጎ አላላውስ በማለት ለትግሉ ወደ ፊት መራመድ ትልቅ ድርሻ የነበረው በወሎ ወልዲያ ቆቦ የተደረገው የሞት ሽረት ትግል ለመሆኑ በቅርበት የምናውቀው ሀቅ ነው።

ባለፉት 50 ዓመታት በሰማውና በተጋጋለው የኢትዮጵያውያን ትግል ላይ የቄሮ አስተዋጽኦ የሚናቅ አይደለም። እውነት ለመነጋገር የቄሮ ትግል ከችግር የጸዳ ነው ማለት አይቻልም። የተወሰኑ የመሀል ፖለቲካን የሚያራምዱ ትንታግ የኦሮሞ ልጆች ትግሉን ቃኝተው ወደ መሀል አመጡት እንጂ መጀመሪያ ላይ አግላይና ሌላውን የኢትዮጵያ ህዝብ የሚጋብዝ አልነበረም። ካልኩሌተሩን የሰራነው እኛ ነን የሚሉ የርቀት ታጋዮች የቄሮን ትግል ጸረ ኢትዮጵያ እንዲሆን ያልፈነቀሉት ድንጋይ እንዳልነበረ እናስታውሳለን። በመጨረሻም የውስጥ ትግል አድርገው ህወሀትን በቁሙ ገድለው ሻምፒዮን በመሆን በወጡት የቲም ለማ አባላት ነገሮች መልክ ባይዙ ኖሮ በቄሮ ስም ይደረግ የነበረው ትግል ለሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ምቾት የሚሰጥ አልነበረም። ይህ እውነት ነው። እወነት መነጋገር አርነት ያወጣልና።

የዘር ፖለቲካ መልካም ውጤት ኖሮት አያውቅም። የዓለም ታሪክ የሚያሳየው፡ በዘመናችንም ካየነው እንደምንረዳው የዘር ፖለቲካ መጨረሻው እልቂት ነው። ሀሳብና እውቀት የነጠፈበት፡ ጥላቻ ምግቡ የሆነው የዘር ፖለቲካ የኢትዮጵያ ትልቁ ፈተና ሆኖ ተደቅኗል። የዘር ፖለቲካ ልቦናን ይጋርዳል። አይንን ያውራል። አዎን! ሚኒሶታ፡ ኖርዌይ፡ ለንደናና አውስትራሊያ ተቀምጠው በቴሌቪዥን መስኮት የዘር ዕልቂት በሚያራግቡ ግልገል ምሁራን እየተፈጸመ ያለው እልቂት ለየትኛውም ወገን የሚበጅ አይደለም። የጥላቻ ማስተላለፊያ በሆነ ቴሌቪዥን ጣቢያ አማካኝነት የሚቀርቡት እንግዶች በተመቻቸ ሀገር ላይ እየኖሩ ለደሀው ህዝብ ቆንጨራና ገጀራ የሚያቀብሉበት ሁኔታ አሳፋሪ የጊዜው ፖለቲካ ሆኗል። የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መንግስት ነገሮችን በሰከነ መልኩ እየተመለከተው መሄዱ ተገቢነት ቢኖረውም ለእንዲህ ዓይነቱ አይን ያወጣ ጋጠወጥ ተግባር ትዕግስት ሊኖረው አይገባም። የህዝቡ ትዕግስት ፍርሃት የመሰለው የዘር ፖለቲካ አቀንቃኝም ቆም ብሎ ሊያስብ ይገባል። የወረወሩት ሰይፉ ዞሮ የት ሊያርፍ እንደሚችል አሁን ላይ ላይታይ ቢችልም ሩቅ ግን አይደለም።

ለማጠቃለል ያህል ቄሮ ለዚህ ድል አበቃችሁ የሚለውን ትርክት አቁሙትና ለእውነተኛ የለውጥ ሂደት በጋራ እንስራ። የቄሮ አስተዋጽኦ ይታወቃል። በልኩ መቁረስ አለበት። ለእኔ ነጻነት በተከፈለው ዋጋ የቄሮ ሚና እንደሚኖር አልክድም። ግን ብቸኛ አይደለም። በቅብብሎሽ በመጣ ትግል የተገኘ የለውጥ ሂደት ነው። ለውጡ እንዲህ እልቂት የሚያመጣ፡ ሀገር የሚያስጣ ከሆነ አንደኛውን በተደራጀ መልኩ መንግስታዊ ቅርጽ ይዞ ሲቀጠቅጥ የነበረው ህወሀት ይሻላል የሚል የህዝብ ስሜት ሊያቆጠቁጥ እንደሚችል አልጠራጠርም። እናም የዘር ፖአለቲካ አቀንቃኞች ከኢትዮጵያ ላይ እጃችሁን አንሱ!!!!

  1. የብሄር ፖለቲካና የስደቅ አላማችን ፈተና !!!

::::::::::::::;;;;;:::::::::::
ኢህአዴግ፤ የብሄር ፖለቲካን በማክረሩ ምን ተፈጠረ? ብዙ በጎሳና በጎጥ የታጠሩ ዜጎችና የፖለቲካ ድርጅቶች እንደ አሸን ከመፍላታቸውም ባሻገር አገሪቱን ለአስከፊ የዘረኝነት አደጋ አጋልጧታል፡፡ ይህንንም አደጋ(የተቀበረ ፈንጂ በሉት::) ዛሬ ከ27 ዓመት የፌደራል ሥርዓት ተሞክሮ በኋላ… በኦሮሚያና በሶማሊያ ክልሎች አስፈሪና አሳፋሪ የዜጎች እልቂትና መፈናቀል ተከስቷል፡፡ (ያውም በገዛ አገራቸው::) አምባገነን የክልል መንግስታትና የጎሳ መሪዎች እንዲሁም የዘር ፖለቲካ ልሂቃን ተፈጥረዋል፡፡ አብጠዋል፡፡

(መካድ ሳይሆን ማረቅ ነው የሚበጀው::) ጎሰኝነት (በዛሬ ቋንቋ “የተለጠጠ ብሄርተኝነት”) እነ አፄ ቴዎድሮስና አፄ ምኒልክ የፈጠሩትን “ኢትዮጵያዊነትንና አንድነትን” አፈር ድሜ አስግጦታል፡፡

(ዕድሜ ለኢህአዴግ::) አያሌ በምንም የማይግባቡ “ዘረኞች” የፌስቡክ ትውልድን አፍርቷል- ኢህአዴግ ሴረኛው::

ሌላውና ትልቁን ፀበ ጫሪነትን ሚያስከትለው ደግሞ
በኢትዮጵያዊነት ላይ ብቻ ሳይሆን በብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ላይ ከስምምነት ላይ ያልደረሰ ህዝብም ፈጥሯል፡፡
ይሄ ድል ነው ውድቀት….?

በወቅቱ ፈላጭ ቆራጭ ከነበሩት ከጠ/ሚኒስተር መለስ አንደበት (“ባንዲራ ጨርቅ ነው” የተባለ ጊዜ ነገር ተበላሸ!) … አምና የሰንደቅ ዓላማ ቀን ሲከበር ስንመለከት ከሃገርአዊ ባንዲራ ይልቅ የድርጅት የክልል ባንዲራ ነበር ሲንፀባረቅ የነበረው::
ባንዲራው
ኢትዮጵያን የሚወክል መሆን ሲገባው አደባባይ ይዘን የምንወጣው ባንዲራ ግን የተደበላለቀ ሆኗል፡፡

የአንድ አገር አይመስልም፡፡ ለደመራ በዓልና ለኦሮሞ የእሬቻ በዓል ህዝቡ ይዞ የወጣውን የባንዲራ ዓይነት መቃኘት ብቻ በቂ ነው፡፡ ግማሹ “ሌጣውን ባንዲራ” ግማሹ ባለ ኮከቡን ግማሹ ደግሞ “የሞሐ አንበሳን” (የንጉሱን ዘመን) ባንዲራ በእሬቻ በዓል ላይ ደግሞ የሚበዛው የኦነግን ባንዲራ ይዞ ነው ሲወጣ ባሳለፍነው አመት ያስተዋልነው:፡

ኢህአዴግና የጎሳ ፖለቲካ አቀንቃኞች (ልሂቃንን ጨምሮ) ለዓመታት የለፉበትን … አበክረው የተጉበትን እኮ ነው እያፈስን ያለነው ጎበዝ …?
(ትላንት የዘራነውን ዛሬ እያጨድን ነው:: በአገር ውስጥ ኢህአዴግና ተቃዋሚ የጎሳ ፖለቲከኞች ከውጭ “ዘረኛ” የኢትዮጵያ ዲያስፖራዎች፤ ላለፉት 27 ዓመታት በአገሪቱና ህዝቧ ላይ ምንድነው ሲዘሩ የከረሙት..? ፍቅርን..? ኢትዮጵያዊነትን..? አንድነትን? የአገር ፍቅር ስሜትን? አገር ወዳድነትን? (አንደኛውም መልስ አይደለም::)
ለዓመታት ብሄርተኝነት እንጂ መች ኢትዮጵያዊነት ተሰበከ? የክልሎች አርማ እንጂ መች ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ደምቆ ተውለበለበ…?
የብሄር ፍቅር እንጂ መች የአገር ፍቅር በውስጣችን ተቀጣጠለ…? (ፌስቡክ ምስክር ነው::)
በዓመት አንዴ በሚከበረው “የብሄር ብሄረሰቦች ቀን” እንኳን ባለፈው ታሪካችን፣ አንዱ ብሄር ለሌላው ብሄር ያደረገው ቅንጣት በጎ ነገር መች ተጠቅሶ ያውቃል?! (የበዳይነትና የተበዳይነት ስሜት እንጂ!)
እንደውም ህዝባችን ጎሰኛ መሪዎችና ፖለቲከኞች የዘባረቁትን ሁሉ ስለማይሰማ ነው እንጂ እስካሁን ተላልቀን ማንም አይተርፍም ነበር፡፡
ግን ደግሞ ይህቺን አገር ፈጣሪ ይወዳታል፡፡ ህዝቡም ጨዋና አርቆ አሳቢ ነው።
ለዚህ ብቻ ነው የተረፍነው፡፡ (ተዓምረኛ አገርና ህዝብ::)

ዛሬ በመዲናችን አዲስ አበባ በአደባባይ ሲንፀባረቅ ያስተዋልነው ከሃገር ይልቅ የመንደር ፓርቲ አርማ ሃገርን የሚወክ ባንዲራ አውርደን የፓርቲ አርማቸውን ካልሰቀልን በሚሉ ብሄርተኞች ነበር ከተማይቱ ስትታመስ የዋለችው እንግዲህ ምን ያክል እየጠበብን እንዳለን እዚህ ጋር መመልከት ይቻላል ::
መንግስት ዝምታውን ሰብሮ ማያዳግም እርምጃ ማይወስድ ከሆነና ይሄ ድርጊት በዚሁ ከቀጠለ ኢትዮጵያ በታሪኳ ተከስቶ በማያቅ ደም መፋሰስ ውስጥ ትገባለች የሚል እምነት አለኝ::
(ጥበብ እንጂ ጉልበት ውጤት የለውም::) የቅሬታ ዕዳዎቻችንን እየቀነስን ለቀጣዩ ትውልድ ቀለል ያለ ሸክም ብናስረክበው ደግ ነው፡፡

ቸር እንሰንብት::

  1. ከኮ/ል ደመቀ ዘውዱ ለአዲሱ ዓመት የተላለፈ መልዕክት!

ለመላው አማራ እና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሳችሁ!

ከሁሉም አስቀድሜ ከእስር ቤትም ከተለያየ ቦታም የነበራችሁ ውድ የአማራ ልጆችና ኢትዮጵያውያን በዓሉን ለማክበር ስለቻልን እግዚያብሔር ይመስገን! በመቀጠልም ተገናኝተን በነፃነት በዓል እንድናከብር ለአስቻሉን ሰማዕታት ክብር ምስጋ ይገባቸዋል።

ወቅቱ የተለያየ ነገር የተቀላቀለበት ነው። ለውጡ መልካም ነገሮች እንዳሉት ሁሉ ያልጠሩም ነገሮች አሉት። በተለይ ለአማራ ሕዝብ ወቅቱ በጥሞና መታየት ያለበት ነው። በሲቪክ ማህበር ስም፣ በፖለቲከኛም ስም የሚመጡ ብዙ ናቸው። እነዚህ አካላት ከአማራው ጥቅምና ጥያቄ አንፃር መታየት አለባቸው። የፖለቲካ ቁማርተኛውን እና እውነተኛውን ተቋም፣ እውነተኛውን አንድነት አካል መለየት አለብን። ከነፈሰው ጋር መንፈስ አያስፈልግም።

አንድነትን እንደግፋለን፣ አንድነትን የምንደግፈው ግነ በምክንያት ነው። አንድነቱንም፣ መደመሩንም የምንደግፈው የአማራውን ጥያቄ እውቅና የሚሰጥ እና የሚመልስ ከሆነ ነው።

ከውጭ የቆዩ፣ በሀገር ውስጥ የተቋቋሙ የአማራ ተቆርቋሪ ድርጅቶች አሉ። አማራ ጥያቄውን ለማቅረብ ብዙ ተቋም አያስፈልገውም። ጠንካራ ተቋም ያስፈልገዋል። ወደፌደራል መንግስቱ፣ ወደ አራት ኪሎ ስንሄድ የምንጠይቀው የአንድ አማራን ጥያቄ ነው። የአንድ አማራን ጥያቄ ለማቅረብ፣ ወደ ፌደራል መንግስቱ፣ ወደ አራት ኪሎም ስንሄድ በአራት ወይም በአምስት አቅጣጫ መጓዝ አይጠበቅብንም። የለብንም። የአንድ አማራን ጥያቄ ለማቅረብ ተቀራርበን ተገናኝተን፣ ተወያይተን፣ መስማማትና መጠንከር ነው የሚገባን። ከመራራቅ ስለ ሕዝባችን ተቀረርበን መስራት አለብን። የአማራ የተበጣጠሰ አደረጃጀት የሚጠቅመው ለሕዝቡ ሳይሆን ለጠላቶች ነው።

አማራ አሁንም መታሰሩ አልቀረለትም። ግድያው አልቀረለትም፣ መፈናቀሉም፣ መበደሉም አልቀረለትም። ዛሬም በወሎ በማንነታቸው እየተገደሉ ነው፣ እየታሰሩ ነው። በወልቃይትና በራያ አማራ በማንነቱ ምክንያት ብዙ በደል እየተፈፀመበት ነው። ይህን ማስቀረት የምንችለው ተቀራርበን፣ በጋራ ስንሰራ ነው። ለአማራው ዘላቂ ሰላምና ጥቅም አብረን፣ ተስማምተን መስራት አለብን።

የአማራውን መደራጀት ሌሎች ብሔሮችም፣ በማንነት ያልተደራጁም ሊቀበሉት ይገባል። እንደራጅ ስንል ራሳችን ለማሰከበር እንጅ ሌሎችን ለመጉዳት አይደለም። ሌሎቹም የአማራን መደራጀት መደገፍ አለባቸው። በማንነት መደራጀት አሁን ባለው ሕገ መንግስት ላይ የተቀመጠና፣ ሌሎች እየተጠቀሙበት መሆኑም መታወቅ አለበት። ሌሎች በማንነት ተደራጅተዋል። እኛ ሌሎች በማንነት ሲደራጁ እንደደገፍን ሁሉ ሌሎቹም የአማራውን መደራጀት ሊያምኑበት ይገባል። ሀገር የጋራ ነች። ሌሎች የራሳቸውን ችግር ለመፍታት እንደተደራጁት፣ አማራም በራሱ ላይ የተደቀነበትን ችግር በመፍታት ለሀገሩም የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲያደርግ መደገፍ አለበት።

ይህን አዲስ አመት እንድናከበር የአማራ ልጆች መስዋዕትነት ከፍለዋል። የኦሮሞ፣ የኢትዮጵያ ልጆች ዋጋ ከፍለዋል። ይህን አዲስ አመት ከእስከዛሬው በተሻለ በነፃነት እንድናከብር መስዋዕትነት የከፈሉት ወንድምና እህቶቻችን ቤተሰቦች ለእኛ ሲሉ የተሰውትን ሰማዕታትን እያሰቡ መቆዘምና ማዘን የለባቸውም። መኩራት ይገባቸዋል። ለዚህ ለውጥ ሲባል የተሰውት ሰማዕታት ቤተሰቦችን ከጎናቸው መሆን ይገባናል። የአማራ ጥያቄዎች እስኪመለሱ ድረስ በሰከነ መልኩ እየተነጋገርን፣ ተባብረን መስራት አለብን!

መጭው ዘመን ለመላው አማራም ሕዝብ እንዲሁም ለመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ የሰላም፣ የመተባበርና የስኬት እንዲሆን ምኞቴን እገልፃለሁ።

ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ

(ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ እኔ እና ጓደኞቼ ዛሬ መስከረም 1/2011 ዓም ወደቤቱ እንኳን አደረሰህ ለማለት በሄድንበት ወቅት ለሕዝብ እንድናደርስለት ያስተላለፈው መልዕክት ነው)

(በ Getachew Shiferaw)

  1. #Ethiopia ||•#Wollo || #Raya

በራያ ዛሬ መላው የዋጃ-ጥሙጋ ወጣቶች አየር ማረፍያን ጨምሮ በትግራይ ክልል ልዩ ኃይል ተፈናቅለው በራያ ቆቦ ወረዳ ሥር በሚገኘው ጮቢ በር አካባቢ ሰፍረው ጊዚያዊ መጠለያ እንድሰጣቸው ለራያ ቆቦ ወረዳ እና ለሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደር ቢያንስ ሰብአዊነት የተሞላው እርዳታ እንኳ እንዲደረግላቸው ጥያቄአቸውን ለሚመለከተው አካል ሁሉ እያመለከቱ ይገኛሉ፡፡
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ይሄ የሆነበት ዋነኛ ምክንያት…
.
1ኛ) ከ5,000 በላይ የሚሆን የተለያዩ የክልሉ ልዩ ኃይሎች እና አድማ በታኞችን ከአየር ማረፍያ እስከ ዋጃ የቆቦ ድንበር ድረስ ያለው አካባቢ ተቆጣጥረው ወጣቱን እያፈሱ ለሰው በላው ማስረከብ ሲሆን ሌላው
.
2ኛ) አሁን በሃገሪቱ የተጀመረው የሰላም;የነፃነትና የአንድነት የለውጥ እንቅስቃስቃሴ ለመጎናፀፍ እና ለመደገፍ ሲሉ ቅስቀሳውን በሚያካህዱ እና የለውጡን ኃይል መሪ በሆኑ ወጣቶች ላይ የማያዳግም ርምጃ ለመውሰድ ከ150 ያላነሱ የዋጃ ጥሙጋ ወጣቶች በፍ/ቤት ማደኛ አውጥተው ሲቭል በለበሱ ልዩ ኃይሎች እያታደኑ ስለሆነ ነው።
.
ለዚህም 4 የአየር ማረፊያ ወጣቶች ታፍነው ተወስደዋል፡፡
በአጠቃላይ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ የዋጃ ጥሙጋ ወጣቶች የአየር ማረፍያን ጨምሮ በጮቢ ቀበሌ አስተዳደር ቅጥር ግቢ ውሥጥ ግዚያዊ መጠለያ ይሰጡናል ብለው ተስፋ የጣሉባቸውን የራያ ቆቦ ወረዳ እና የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደር እንዲያወያይዋቸው እና ግዚያ መፍትሄ እንድሰጧቸው ተሰብስበው በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ፡፡
የጮቢ በርና አካባቢ ነዋሪዎችም አይዟችሁ አጠገባችሁ ነን የመጣውን ሁሉ አብረን እንጋፈጣለን በማለት በደስታ ተቀብለዋቸዋል፡፡
ፍትህ ለራያ ሕዝብ! Jano Arbise

Via መጋዝ Brook Abegaz Aba Bona

  1. የአመቱ ምርጥ ኮሜንት!!!

ይህ አስተያየት የተሰጠው ለእቴጌ ጣይቱ ሐውልት የመሰረት ዲንጋይ ለመጣል ከተዘጋጀ በሁዋላ በኦሮሞ አክቲቪስቶች ጫጫታ የተነሳ የመሰረት ድንጋዩ ሳይጣል መቅረቱን ተከትሎ በOMN በተሰራ ዘገባ ስር @YAYESHHULU YINBEREKEKILISHAL በመሚል አካውንት የተሰጠ አስተያየት ነው*****
#እንደዚህ_ይላል……..
1.እውነት ለመናገር እኛ ኦሮሞዎች ጥበብ እና ጀግንነት አይወድልንም: : ጠበብን እና ጀግነትን ተገንዝበን አያከብርም:: ጣይቱም ትሁን ምንሊክ ከ50% በላይ ኦሮሞ ናቸው:: ነገር ግን ኦሮሞ ሞኝ ነን ; ብዙ ግዜ በ inferiority compex ወደ ሃላ እንቀራለን:: አማራ የወደደው እና ያደነቀው ነገር ሁሉ የአማራ ይመስለናል:: በዚህም ጀግኖቹን እና ጠቢባኑን መጠቀም ሳይችል: ;ለሌሎች አሳልፎ ይሰጣ ; ጀግኖቻችን እና ጠቢባኖቻችን በሌሎች hijacked ይደረሉ::

2.አማራ ብልጠቱ ከየትም ብሄር ብትሆን ; ጀግና እና ብልህ ወይም አዋቂ ከሆንክ ይወድሃል:,ያከብርሃል የራሱ እስክትመስለው ያቀርብሃል:: Because they give high values for knowledge , wisdoms, leadership and heroism . ሞኝ ,ተላላ , አላዋቂ , ፈሪ ከሆነ አማራ የራሱንም መሪ ቢሆን አያከብርም አያደንቅም::

3. በትንሹ ለምሳሌ መንግስቱ ሀይለማሪያም በእናቱም ይሁን በአባቱ ኦሮሞ ነው ; የሚወደው እና ሚደነቀው ግን በአማራ ነው:: ሌሎችም እጅግ ብዙ አሉ እንደእነ ሎሬት ፀጋየ ገ/መድህንም 100% ኦሮሞ ናቸው ; በጥበባቸው የሚወደዱት እና ሚከበሩት ግን በእማራው ነው::

4.እዩዋቸው አቢይ አህመድ እና ለማ መገርሳን ; አማራ እንዴት እንዳነገሳቸው ,እንደወደዳቸው, እንዳከበራቸው , ህይወቱን አሳልፎ እንደ ሚስጥላቸው ::

5. እነሱ ግን ከኦሮሞ እናት እና አባት ተገኝተው , የኤሮሞን ወተት እና ውሃ ጥጥተው አድገው ሳለ ; አማራ ያየው ብሄራቸውን አይደልም ; ድፍረታቸውን ,leadership አሰጣጣቸውን , ብልህነታቸውን እና ቅንነታቸውን ነው:

6. የኦሮሞ ችግሩ በድሮው አባገዳ ደረጃ የሚወደሰውን እና የሚደነቀውን ; ከብት ጠባቂ ጀግና(0ld fashion warriors)ወይም local heroes እንጅ ; ለnational ጀግና ክብር አይሰጥም:: በዚህም የተነሳ የኦሮሞ ተወላጅ ዘመናዊ መሪዎቻችንን ብዙ እርቀት ሄደው ሀገር የመምራት እንዳይችሉ እንቅፋት እንሆናለን::

7. አሁን ለምሳሌ ኦሮሞ ቄሮ ጅዋር መሃመድ እንወድዋለን እናከብረዋለን እንበል; ጅዋር መሀመድ በ National ደረጃ በአማራ እና በትግራይ በሌላውም ብሄር ተቀባይነት ቢኖረው ; እኛ ኦሮሞዎች ጅዋር ኦሮሞ አይደለም እንላለን ; ምክንቱም ጅዋር local ብቻ ሆኖ ; ኦሮሞ ኦሮሞ እያለ ብቻ እንዲቀር እንፈልጋለን::

8. ለዚህም ነው ምእራብያውያን ; የአንድን ማህበረሰብ ስነልቦና እና የእውቀት ደረጃ ; ወይም values ለማወቅ ወይም ለመረዳት ከፈለግክ ; ማህበረሰቡ የሚያደንቃቸው ጀግኖቻቸውን ወይም icons ቸውን ቀርበህ ተመልከት ወይም አድምጥ የሚሉት::

9. ምሊክንም ይሁን ጣይቱን ያስተዳደሩት ትምህርት በሌለበት ,ሚድያ በሌለበት ,ፌስቡክ በሌለበት የዛሬ 200 አመት ነው ; ስለዚህ በድሮው ዘመን የንጉሳዊ አገዛዝ አስተሳሰብ እንዳኛቸው::

እንግሊዝ አውሮጳም ቢሆን በዚያ ዘመን ; አንድ ግዛት አልገብርም ብሎ ካስቸገረ ; ለምን የእናቱ ልጆች አይሆኑም ; ለ 2 ግዜ ወይም 3 ግዜ ማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ከንጉሱ ከቤተመንግስት ይላክ እና ; አሁንም አሻፈረኝ ካለ ተንቂያለው ብሎ የማስፈራሪያ እርምጃ ; አልገብርም ብሎ ባስቸገረው በግዛቱ ህዝብ ላይ ይወሰድበት ነበር: “”nothing is personal or hatred”

10. እነሱ አልከተልም ወይም አልገብርም ያላቸውን ህብረተሰብ ; እንደነ ጅዋር 6 አመት ሙሉ በፌስቡክ ህዝብን ለማሳመን ; እንደ ለማ መገርሳ ለማግባባት ምንም ዘመናዊ የመረጃ ማስተላለፊያ እና ሚድያ ሳይኖራቸው ; ሰው ቢገድሉ ወይም ቢያስፈራሩ ምን ይገርማል ;

እኛ አለን አይደል በዘመናዊው ዘመን ተምረን እና ተፈጥረን የዛሬ 20 ቀን ; የደቡብ ልጅ እንደኛ ኦሮምኛ አልተናገረም ብለን ;በዚህ በሰለጠነ ዘመን በኮምኔኬሽን ማሳመን አቅቶን inocent ሰው ሻሸመኔ ላይ ዘቅዝቀን የገደልን እና ያቃጠልን:: በምንሊክ ከተናደድን እኮ ከምንሊክ መማር ነበረብን; እውነተኛ ከሆን where is our practical justification ?

Let’s set our standards higher and push forward our Oromo leaders to the national and global levels by admiring them. ር ል

  1. በአማራ ክልል ቴሌቪን አቶ ሙሉዓለም ገሌ

ቀርበው በሰጡት ቃለምልልሰ ለሱዳን ስለተሰጠው መሬት አቶ ሙሉዓለም ገሌ በሀቅ እንደገለፁት በወቅቱ የፈደራል ጉዳዮች ባለሥልጣን የነበሩት አቶ አባይ ፀሐይ እንደሰጡ በማሰረጃ አረጋግጠዋል ፡፡ ሕወሀት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ በተለይም በአማራ ሕዝብ ላይ ታሪክ ይቅር የማይለው በደል ተፈፅማል ፡፡ ወያኔ አሰብን ለኢርትራ ያለምንም ህፍረት ሰጥቶ የኢትዮጵያን ሕዝብ ወደብ አልባ አድርጎ በደህነት ለዘላለም እንደማቅቅ አድርጎአል ፡፡ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሳማክሩ የአማራ ክልል መንግስት ሳያውቀው አቶ አባይ ፀሐይ ለሱዳን የሰጡት መሬት በአማራ ጀግና ገበሬ ይመለሣል ፡፡ ወያኔ መቀበሪያውን የሚቆፈረው በራሱ በወያኔ ባለስልጣን ነው ፡፡
ለአማራ ክልል ባለስልጣን የማስተላልፈው መልክት ለአቶ ሙሉዓለም ገሌ ልዩ ጥበቃ ማድረግ አለበት ለሱዳን ሰለተሰጠው መሬት ጠንቅቀው ሰለሚያውቁ ወያኔ ልክ እንደ ኢንጅነር ስመኘው በቀለ ሊገድሉአቸው ይችላሉ ፡፡ ወያኔ ሰዎችን በመግደል መረጃ በማጥፋት ሥልጣኑን ለማቆዬት ከበረሀ ጀምሮ እስካሁን ቀጥሎአል ፡፡
አቶ በረከት ስምዖን ሌባው ለወያኔ አለቆቹ ለማስደሰት የአማራን ሕዝብ ሲያዋርድ ኖሮአል ፡፡ አሁንም ወያኔን ለማሰደሰት በማያፍር አደበቱ የአማራ ክልል ባለሥልጣንን እየተሳደበ ነው ፡፡ በጣም የሚያሳዝነው አቶ በረከት መጽሐፍ ጽፌአለሁ ይላል ፡፡ ሌባ በምን ታሪክ ተመስርቶ ነው መጽሐፍ መጻፍ የሚችለው ፡፡ የማፍያ ቡድን የበረከትን መጽሐፍ ገዝቶ የሚያነብ ካለ ጥሩ ሌባ ለመሆን ምኞት አለው ማለት ነው ፡፡ የአማራ ክልል ሕዝብ አቶ አባይ ፀሐይ ባሰቸኩይ ለፍርድ እንድቀርብ መጠየቅ አለበት ፡፡ የአማራ ክልል መንግስት ዜጎችን ከወያኔ ተኩላዎች መጠበቅ አለበት ፡፡ በተለይ አቶ ሙሉዓለም ገሌ ጥበቃ ሳይደረግ ቀርቶ የወያኔ ተኩላ ቢበላቸው የአማራ ክልል መንግሰት ተጠያቂ ነው ፡፡ አቶ ሙሉዓለም ገሌ ለእኔ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ሀገር እና ሕዝብ ወዳድ ጀግና ኢትዮጵያዊ ነዎት ፡፡ ዘመንዎን ከሙሉ ጤና ጋር እግዚአብሔር ይባርክልዎት ፡፡
ሀቀኛ ሰው ሀብት ሊኖረው አይችልም የእርስዎ ሀብት የያዙት ሀቅ እና ሕዝብ ነው ፡፡ በተለይ የሁመራ ሕዝብ ስለሀቀኝነትዎ ያከብርዎታል ይወድዎታል ፡፡